ቡሩንዲ ፌስታሎች በፈረንጆቹ 2020 ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ልታግድ ነው

68
ነሃሴ 8/2010 ቡሩንዲ ፌስታሎች በፈረንጆቹ 2020 ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ልታግድ መሆኑ ተገለጸ ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በሀገሪቱ የፕላስቲክ ምርት የሆኑ ፌስታሎች፣ ማሸጊያዎች እንዳይመረቱ፣ ከውጭ እንዳይገቡ፣ በመጋዘን እንዳይከማቹና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መመሪያ አስተላልፈዋል። በትናንትናው ዕለት የሰጡት መመሪያም በ18 ወራት ውስጥ ገቢራዊ እንደሚሆን ነው የተነገረው። በመሆኑም የፕላስቲክ ፌስታሎችና ማሸጊያዎችን የሚያመርቱም ሆነ ለሽያጭ በመጋዘን ያከማቹ አካላት እርምጃ ከመጀመሩ በፊት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልጉ ቀነ ገደብ ተቀምጠላቸዋል። በፕሬዚዳንቱ መመሪያ ክልከላው ከማይመለከታቸው የፕላስቲክ ምርቶች መካከል የሚበሰብሱ የፕላስቲክ ከረጢቶች፣ በህክምና ተቋማት አገልገሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ምርቶች፣ በኢንዱስትሪና በመድሃኒት መቀመሚያ ተቋማት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች ይገኙበታል። ሞሮኮ፣ ሩዋንዳ እና ኬንያን ጨምሮ በዓለም ከ400 በላይ ሀገራት የፕላስቲክ ፌስታሎችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከልክለዋል። ምንጭ፦ቢቢሲ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም