ፍርድ ቤቱ በሰኔ 16 የቦንብ ጥቃት ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲለቀቁ አዘዘ

92
አዲስ አበባ ነሓሴ 8/2010 በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት የተጠረጠሩ የፍትህ አካላት በዋስትና እንዲለቀቁ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ከቆዬ በኋላ አቃቤ ህግ "በዋስትና ቢለቀቁ ስራዬ ላይ ጫና አይፈጥሩም" በመላቱ ዛሬ ፍርድ ቤቱ  በዋስትና እንዲለቀቁ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ መሰረት አንደኛ ተጠርጣሪ የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከሁለተኛ እስከ ድስተኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ9ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጡ ተፈቅዷል። እንዲሁም ሰባተኛና ስምንተኛ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ6 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የተደረገ ሲሆን ዘጠነኛ ተከሳሽ ደግሞ በ7 ሺህ ብር ዋስትናው ተፈቅዷል። በሌላ በኩል 10 ኛ እና 11ኛ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ9 ሺህ ብር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። በዚህም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን አጠናቆ ወደ መዝገብ ቤት መርቶታል። አቃቤ ህገ አጣርቶ በተከሳሾቹ  ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መረጃ  ካገኘ ክስ ሊመሰረት እንደሚችልም አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም