ከአማራ ክልል የተውጣጡ ባለሃብቶች ለአፋር ክልል 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

258

ጳጉሜ 2/2013(ኢዜአ) ከአማራ ክልል የተውጣጡ 8 ባለሃብቶች ለአፋር ክልል 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

ባለሃብቶቹ ያደረጉትን ድጋፍ ሠመራ ከተማ በመገኘት ዛሬ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።

የተደረገው ድጋፍም አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ባደረሰው ትንኮሳ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እና የጸጥታ ሃይሉን ለማጠናከር የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል።

ባለሃብቶቹ በአፋር ግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የበዓል መዋያ 400 በሬዎችን ድጋፍ አድርገዋል።