በመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

131

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2013 (ኢዜአ) በመስከረም 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሓሴ 2013 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሃሴ 2013 ዓ.ም ሲሸጥበት በነበረው ይቀጥላል።

የዓለም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በየወሩ በመጨመር ላይ ቢገኝም መንግሥት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ ለማስቀጠል ሲል በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል አድርጓል ብሏል መግለጫው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም