በአሸባሪው ህውሃት ላይ በሚካሄደው ዘመቻ የማህበረሰቡ ድጋፍና እገዛ የላቀ ነው

270

ነሀሴ 30/2013 (ኢዜአ) በአሸባሪው ህውሃት ላይ በሚካሄደው ዘመቻ የማህበረሰቡ ድጋፍና እገዛ የላቀ መሆኑን በማይፀብሪ ግንባር የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ።

የአከባቢው ማህበረሰብ ግንባር ድረስ በመዝመት ስንቅ በማቀበል፣ የጦር መሳሪያዎችን ከቦታ ቦታ እያንቀሳቀሰ በማገዝ ለሰራዊቱ ድጋፍ እየደረገ ይገኛል።

በማይፀብሪ ግንባር ከሁሉም አካባቢዎች ሴት ወንድ፤ ወጣት አዛውንት ሳይለይ ሰራዊቱን በማገዝ አሸባሪው እንዲደመሰስ ማህበረሰቡ የነበረው ሚና የላቀ መሆኑን አመራሮቹ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ የአካባቢው ማህበረሰብ በቁርጠኝነት ተዋግቶታል ብለዋል።

ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም በርካታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች መደምሰሳቸውንና መማረካቸውን ተናግረዋል።

የአሸባሪ ቡድኑ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች መማረካቸውን አስታውሰው በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል ብለዋል።

የትግራይን ወጣቶችን ወደ ጦርነት በመማገድ ህይወታቸውን እንዲያጡ በማድረግ በክልሉ ነዋሪ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል መፈፀሙንም ነው የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች የገለጹት።

በቀጣይ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ከእልቂት ለመታደግ አሸባሪውን ህወሃት ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።