የአረንጓደ አሻራ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት ተከናወነ

1014

ነሀሴ 30 /2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የዘንድሮውን የአረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር ማጠቃለያ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ተከናውኗል።

በመርሃ ግበሩ ላይ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ነው የተካሄደው።

የዘንደሮው የአረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተከናወነው።

በዚህም ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥም ሆና በዜጎቿ ጥረት የችግኝ ተከላው በስኬት ተከናውኗል ነው የተባለው።

በኢትዮጵያ ባለፉት ሶሰት ዓመታት 18 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን መረጃዎች ያሳያሉ።