በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበው ስኬት ኢትዮጵያ ያሰበችውን ሁሉ ማሳካት እንደምትችል ማሳያ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

747

ነሐሴ 30 /2013 (ኢዜአ) “በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበው ስኬት ኢትዮጵያ ያሰበችውን ሁሉ ማሳካት እንደምትችል ማሳያ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።

የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ተከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዜጎች ለአረንጓዴ አሻራ ያሳዩትን ቁርጠኝነት በሌሎች መስኮችም ሊደግሙት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን ጠቅሰው፤ “በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበው ስኬት ኢትዮጵያ ያሰበችውን ሁሉ ማሳካት እንደምትችል ማሳያ ነው” ብለዋል።

በመሆኑም “የትኛውም ፈተና ሳይበግረን የኢትዮጵያን ልማትና ብልጽግና እናረጋግጣለን” ሲሉም ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው “የገጠሙንን ፈተናዎች እጅ ለእጅ ተያይዘን በመሻገር የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ አለብን” ብለዋል።