የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሴቶች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ስንቅ አዘጋጁ

58

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 29 ቀን 2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሴቶች አደረጃጀት ለአገር መከላከያ ሰራዊትከ 1ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን  ስንቅ አዘጋጁ።

የደም ልገሳ መርሃ ግብር ያከናወኑት የክፍለ ከተማው ሴቶች ከስንቅ ዝግጅቱ በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመሄድ  'በምንችለው ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን እንሰለፋለን' ብለዋል።

ወይዘሮ ፋጡማ አለም ለሠራዊቱ ስንቅ ማዘጋጀት ብቻ በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው 'እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ በመክፈል ለአገሬ የምችለውን አደርጋለሁ" ነው ያሉት።

አገር ከሌለ እኛም አንኖርም በመሆኑም አገራችንን ማስከበር አለብን ያሉት ወይዘሮዋ የተለያዩ አገራት ኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን ጫና በጋራ እንመክታለን ብለዋል።

የአገር አለኝታ ለሆነው ሠራዊታችን ያለንን ፍቅር እና ከጎኑ መሆናችንን ለማሳየት ስንቅ አዘጋጅተናል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ዘነበች ኃይለማሪያም ናቸው።

ከስንቅ ዝግጅት በተጨማሪ ወጣቶች ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ እያበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መስራትም፣  ሀብት ማፍራትም  እንዲሁም ተረጋግቶ መኖር የሚቻለው አገር ሲኖር ነው ያሉት ወይዘሮ ዘነበች የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ተግባር ለማስቆም ከሰራዊቱ ጎን መቆም አለብን ብለዋል።

ወይዘሮ ትዕግስት ግርማ በበኩላቸው ከአገር የሚበልጥ ነገር የለምና "ግንባር ድረስ በመሄድ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ወስኛለሁ" ነወ ያሉት።

"እኔ ልጆቼን ጥዬ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ ልጆቼን ወገኖቼ ያሳድጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ሌሎችም እንዲሳተፉ አበረታታለሁ ብለዋል ወይዘሮ ዘነበች።

የክፍለ ከተማው ሴቶቹ ያዘጋጁት ደረቅ ምግብ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የክፍለ ከተማው የሴቶች ሊግ ኃላፊ ወይዘሮ ሳይዳ ቃሲም ገልጸዋል።

ሴቶቹ ቀደም ሲልም ለሠራዊቱ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸወን ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፈቲያ መሐመድ ባንዳዎች አገር ለማፍረስ ቢንቀሳቀሱም በሕዝባችን አንድነት ያለሙት አልተሳካላቸውም ብለዋል።

በአገሩ ሉዓላዊነት የማይደራደረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ አገር ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪውን ቡድን በጋራ እየተከላከለ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ያለፉት ዘመናት የኢትዮጵያዊያን ታሪክም ይህንኑ ያመላክታል፤ ዛሬም በየትኛውም አቅጣጫ ጠላትን አሳፍሮ እየመለሰ ይገኛል ነወ ያሉት።

በክፍለ ከተማው ለአገር መከላከያ ሠራዊት በመጀመሪያ ዙር 86 ሚለዮን ብር፣ በሁለተኛው ዙር እስከአሁን 70 ሚለዮን ብር መሰባሰቡን ወይዘሮ ፈቲያ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም