በአዲስ አበባ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች ሊከበሩ ነው

326

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28/2013(ኢዜአ) በአዲስ አበባ የመጪው አዲስ አመት መዳረሻ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች የሚከበር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ኮሙንኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አብዲ ፀጋዬ፤ የጳጉሜን ቀናቶች እና የ2014 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የጳጉሜን ቀናቶች የተለያዩ መሪ ሃሳቦችን አንግበው የሚከበሩ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም መሰረት፡

ጳጉሜን 1 የኢትዮጲያዊነት ቀን

ጳጉሜን 2 የአገልጋይነት ቀን

ጳጉሜን 3 የመልካምነት ቀን

ጳጉሜን 4 የጀግንነት ቀን

ጳጉሜን 5 ቀን የድል ቃል ኪዳን ብስራት ቀን የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

በመሆኑም ሁሉም ቀናቶች በኢትዮጵያዊ እሴቶች ደምቀው የተለያዩ ተግባራት ይከወንባቸዋል ብለዋል።

እነዚህ ቀናቶች ኢትዮጵያ አሁን እያጋጠማት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎችን በመቋቋም ልማታችንን ለማስቀጠል ነው ብለዋል።

መርሃ ግብሮቹ “አዲስ አበባ የኢትዮጵያ የድል ነፀብራቅ” የሚል አጠቃላይ መሪ ሃሳብ እንዳለው አስረድተዋል።