የህልውና ዘመቻው በኢኮኖሚው ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ስትራቴጂ ተቀይሷል

312


ነሀሴ 27 ቀን 2013 (ኢዜአ) በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው የህልውና ዘመቻና ጦርነት ሀገሪቱ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን እና የታክስ መሰብሰቢያ ማእከላትን በማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተዘጋጀው ሳምንታዊ መግለጫ ላይ የሀገሪቷን ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በወቅቱ እንደገለፁትም ጦርነቱ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የገቢ መሰብሰብ አቅም እንዲጨምር ተደርጓል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት በቅርቡ ለምግብና ለሌሎች ወጪዎች 9 ቢሊየን ብር ወጪ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገር ውስጥና በውጪ የሀገር ህልውና ዘመቻን አጀንዳው ማድረጉም ያለውን የትብብር መንፈስ ያጠናከረና የችግር ግዜን ለመውጣት ያስቻለ ነውም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችውና ሚሊየኖች የተሳተፉበት ምርጫም የሃገራዊ አንድነትን አመላካች ነው፡፡
በቀጣይ አመት ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ስራ ይቀጥላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የገቢ ማሰባሰብ አቅምን ማሳደግ፣ ምርታማነትንና የካፒታል ገበያን ማስፋፋት፣ ፕራይቬታይዜሽን ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡