የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ወደ ፀሃይ ሳተላይት አመጠቀ

161
ነሃሴ 6/2010 የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ የፀሃይን የቆዩ ምስጢራዊ ባህሪያት ለመመርመር የሚያስችል ሳተላይት አመጠቀ፡፡ የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ያመጠቃት ሳተላይት ከአሁን በፊት ከተላኩት ሳተላይቶች በበለጠ ለፅሃይ ቅርብ የሆነች ሳተላይት ናት ተብሏል፡፡ ከፍሎሪዳ ኬፕ ካናቬራል የፓርከር ምርምር ጣቢያ ዛሬ የመጠቀችው ሳተላይቷ ከአሁን በፊት ወደፀሃይ ከመጠቁት ሳተላይቶች ፈጣን መሆኗንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ዴልታ-ቲቪ የሚል ስያሜ የተሰጣት ሳተላይቷ የፀሃይን የቆዩ ምስጢራዊ ባህሪያትን ለመመርመር እንደሚያስችላት ተገልጿል ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም