አሸባሪው ህወሃት በአዲአርቃይ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ አራት ሰዎችን ገድሏል

142

ነሐሴ 21 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በአዲአርቃይ ከተማ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በተኮሰው ከባድ መሳሪያ ከአንድ ቤተሰብ ውስጥ አራት ሰዎችን ገድሏል።

የአሸባሪው ቡድን ጥቃት ሰለባ የሆነው ቤተሰብ አባል ወይዘሮ አገሬ መኮንን እንደገለጹት፤ ጥቃቱ የአምስት ዓመት ዕድሜ ያለው የወንድማቸው ልጅ ተገድሏል።

ወይዘሮ አገሬ መኮንን በጥቃቱ መነኩሴ እናታቸውን፣ የግንባታ ባለሙያ ወንድማቸውን ከነባለቤታቸውና የአምስት አመት ህጻን ልጅ ህይወታቸው ተነጥቋል።

ከቤተሰቡ በተጨማሪ ሁለት የጎረቤት ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ ሆነው ህይወታቸውን እንዳጡ ወይዘሮ አገሬ ተናግረዋል።