የአሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ በጅንካ ከተማ እየተካሄደ ነው

ጅንካ ነሀሴ 21/2013 (ኢዜአ) መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና አሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ በጅንካ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሰልፉ ላይ የጅንካ ከተማና ከደቡብ ኦሞ ዞን ወረዳዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ነው።

ሰልፈኞቹ  ህወሃትና ሸኔ ያለ ሀፍረትና ያለ እረፍት ሀገር ለማፍረስ ሲተባበሩ እኔ ሀገሬን ለማዳን የማልተባበርበት ምንም አይነት ምክንያት የለም! የሀገርን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት አሸባሪ ቡድኖቹን እየተቃወሙ ነው።

እኔ የጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደጀን ነኝ ! ደማችንን ህይወቱን ለሚገብረው ሰራዊታችን የሚሉና መሰል መፈክሮችንም በማስተጋባት ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ እየገለጹ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም