አሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

346

አርባምንጭ፤ነሀሴ 21/2013(ኢዜአ) በጋሞ ዞን አሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔን የሚያወግዝና መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከጋሞ ዞን 14 ወረዳዎችና 6 የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አባት አርበኞች፣ በክብር የተሰናበቱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአርባ ምንጭ ሁለገብ ስታሰዲየም እያካሄዱ  ናቸው።

ወጣቶቹ በተለይ “ከአባቶቻችን የተረከብናትን ኢትዮጵያን ክብሯን አስጠብቀን ለመኖር አሸባሪዎችን በግንባር ለመፋለም እንዘምታለን” በማለት ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡

“ከእንግዲህ አሸባሪዎችን እንኳን ሰው የኢትዮጵያ አየር አይቀበላቸውም፣ የአሁኑ ትዉልድ የአባቶችን አደራ አይጥልም፣ አንድነት፣ አብሮነትና ሰላም ለአገራችን ይሁን፣ የአብሮነት ጉዞአችን በአሸባሪዎች አይደናቀፍም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ህዝቡ በአርባምንጭ ከተማ ጎዳናዎች በመዘዋወር ወደ ሰቴዲዮም እየገባ ይገኛል።

በሰልፉ ላይ ለመከላከያ ሠራዊቱ የዞኑ ህዝብ በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እንደሚያደረግም ተጠቁሟል።