አሸባሪው ህወሃት የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ ነው

86

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 18/2013 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን ሀገርን ለማፍረስ የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ አስታወቁ።
ለሀገር ማዳን ዘመቻው እስካሁን ከ29 ኩንታል በላይ እህል፣ ከ6 ሺህ 800 በላይ የእርድ እንስሳትና 14 ሺህ 450 ሊትር ዘይት ተሰብስቧል።

ዶክተር ሙሉነሽ ዛሬ በሰጡት  መግለጫ እንዳሉት፤ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት ህብረተሰቡ ሃብት በማዋጣትና ወደ ግንባር በመዝመት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚያበረታታ ነው።

አሸባሪ ቡድኑ  በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ላይ የተከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ  በአሸናፊነት ለመወጣት የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።

ጦርነቱ በድል ከተጠናቀቀ በኋላ የወደሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትና ተፈናቃይ ወገኖችን  መልሶ ለማቋቋም ቀጣዩ ተግባር እንደሚሆንም አብራርተዋል።

አሸባሪው ህወሃት በከፈተው ጦርነቱ ሳቢያ በአማራ ክልል ከ480 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም