ሩሲያ ኢትዮጵያዊያን የእግር ኳስ ደጋፊዎች የዓለም ዋንጫን ለመመልከት ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቀደች

57
  አዲስ አበባ ግንቦት 8/2010 በሚቀጥለው ወር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ኢትዮጵያዊያን የእግር ኳስ ደጋፊዎች ያለ ቪዛ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ አዘጋጇ አገር ሩሲያ ፈቀደች። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው የዓለም ዋንጫን ለመታደም ወደ ሩሲያ መሄድ የሚፈልጉ ደጋፊዎች ህጋዊ ፓስፖርትና የደጋፊ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቪዛ ሊታደሙ ይችላሉ። በዚሁ መሰረት የዓለም ዋንጫ ዝግጅትን በሩሲያ ተገኝቶ ለመመልከት የእግር ኳስ አፍቃሪ ቤተሰብ የደጋፊ መታወቂያ www.fan­-id.ru በሚለው ድረ-ገጽ ላይ በመመዝገብ ማግኘት እንደሚችል ጠቁሟል። ዓለም በጉጉት የሚጠብቀውና 32 አገራት የሚሳተፉበት የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከሰኔ 7 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ ለአንድ ወር ይካሄዳል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም