የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል

ነሃሴ 5-2013 (ኢዜአ) የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ከአጋር አሃዱዎች ጋር በመሆን በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡በሂደቱ በርካታ የጁንታው አሸባሪ ቡድን አባላት ተደምስሰዋል ፡፡
በዚህም 35 የጁንታው አሸባሪ ቡድን አባላት ተማርከዋል ከተማረኩት መካከልም ከ18 አመት በታች የሚሆኑ 20 ህፃናት የሚገኙበት ሲሆን 15 ደግሞ ከ18 እስከ 25 ዓመት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ ሃላፊ ኮ/ል ጉደታ ኦፍጋአ ፣ የጁንታው አሸባሪ ሃይል በአፋር ክልል ጭፍራ ግንባር በኩል የመጣውን የጁንታው አሸባሪ ቡድን ከሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል እንዲሁም ከልዩ ዘመቻ ጋር በመሆን ድባቅ መመታቱን አረጋግጠዋል ፡፡የምስራቅ ዕዝ ዘመቻ ሃላፊ ኮ/ል ጉደታ ኦፍጋአ የኢትዮጵያ ህዝብ አሸባሪው ጁንታ በሚያስራጨው የሃሰት ወሬ መደናበር የለበትም ነው ያሉት፡፡
ሃላፊው አክለውም የሚወራው እና በተግባር የሚታየው በምንም የማይገናኝ ስለሆነ ህዝባችን አንድነቱን በማጠናከር ለሰራዊቱ እያደረገው ያለውን ድጋፍ በማጠናከር መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ከተማረኩ የጁንታው የሽብር ቡድን አባላት መካከል ለትሽ ሃድጉ ፣ ጁንታው በማስገደድ ወደ ወጊያ እንዳስገባት እና በሷ እድሜ ክልል ከ18 አመት በታች በርካታ ህፃናትን በማስገደድ እና በማስገባት ትግራይን ያለ ወጣት እያስቀራት መሆኑን ተናግራለች፡፡
ሸዊት ፍትዊ በሰጠው አስተያየት የጁንታው አሸባሪ ቡድን ከመንገድ ላይ አፍሶ ወደ ውጊያ በግድ እንዳስገባቸው ገልፆ ፣'' ከተማረኩኝ በኋላ እነሱ ካሉት በተቃራኒ የመከላከያ ሰራዊታችን በእንክብካቤ በማከም ምግብ እና ውሃ በመስጠት ነፍሴን ታድጎኛል'' ብሏል፡፡ምንጭ-የሀገር መከላከያ ሰራዊት