በሊጉ የዛሬ ጨዋታ ጅማ አባቡና ዲላ ከተማን አራት ለአንድ አሸነፈ

58
ጅማ ነሃሴ 2/2010 በ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዛሬ ጨዋታ ባለሜዳው ጅማ አባቡና ዲላ ከተማን አስተናግዶ አራት ለአንድ  በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ለጅማ አባቡና የማሸነፊያ ጎሎቹን ያስቆጠረው በአምስተኛው ፣በ22ኛው እና42ኛ ደቂቃ በብዙአየሁ እንዳሻው እንዲሁም በ89ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ በተመስገን ደረሰ አማካኝነት ነው፡፡ ብዙአየሁ ሃትሪክ ከመስራቱም በላይ  ለተጋጣሚው ዲላ ከተማ ተከላካዮች ፈተና ሆኖ ታይቷል፡፡ በ72ኛ ደቂቃ ላይ ደግሞ የዲላ ከተማ በረኛ ከመስመሩ ውጭ ኳስ በመንካቱ በረኛው በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡ የዲላ ከተማ ተጫዋቾች በረኛው በቀይ ካርድ ከውጣ በኋላ ሙሉ በሙሉ በሜዳቸው መከላከል ላይ በማተኮር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ጅማ አባቡና ከረፍት በኋላጨዋታቸውን በማቀዝቀዝ በ52ኛ ደቂቃ ላይ ዲላ ከተማዎች እድሉን ተጠቅመው ከባዶ ከመሸንፍ ያዳናቸውን ጎል በሙና በቀለ አማካኝነት ማስቆጠር ችለዋል፡፡ ጅማ አባቡና ማሽነፉን ተከትሎ የከፍተኛው ሊግ የምድብ "ለ" በ53 ነጥብ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት የሚያደረገውን ግስጋሴ አጠናክሯል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሃትሪክ የስራው ብዙአየሁ እንዳሻውም በ17 ጎል የከፍተኛ ሊግ የኮከብ  ጎል አስቆጣሪነቱን ደረጃ  እንዲያጠናክር አስችሎታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም