ሰላምና አንድነታችንን ጠብቀን ሉአላዊነታችንን እናረጋግጣለን!

ደሴ፤ ሐምሌ 23/2013(ኢዜአ) ለአሉቧልታ ወሬ ቦታ ሳንሰጥ ሰላምና አንድነታችንን ጠብቀን ሉአላዊነታችንን እናረጋግጣለን!
ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴ ከተማ  የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና አሸባሪውን የህወሃት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ አሸባሪውን የህወሃት ቡድን ለመደምስስ ዝግጁ ነን፣ አሉቧልታ ወሬ ቦታ የለውም፣ ሰላምና አንድነታችንን ጠብቀን ሉአላዊነታችንን እናረጋግጣለን  ሰልፈኞቹ ካስተላሉት መልዕክት መካከል ይገኙበታል።

ሀገር አፍራሾች ይፈርሳሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ የህዳሴ ግድቡ እንዲጠናቀቅ የድርሻችንን እንወጣለን፣ የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ይቁም ሲሉ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

ከዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ወጣቶችና ሴቶች  በሰልፉ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም