የሁርሶ ኮንቲጀንት ትምህርት ቤት መሠረታዊ ወታደሮችን እያስመረቀ ነው

62

ሐምሌ 17/2013 (ኢዜአ) በመከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ትምህርት ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች እያስመረቀ ነው።

በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው አንጋፋው የሁርሶ የሰላም ማስከበር ማዕከል በክብር እንግድነት ተገኝተው መሠረታዊ ወታደሮችን እየመረቁ የሚገኙት የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ናቸው።


በመሠረታዊ ወታደርነት የሰለጠኑት ወታደሮች በቆይታቸው የቀሰሙትን ወታደራዊ ጥበብና ዕውቀት በተግባራዊ ትዕይንት ለክብር እንግዶች እያሳዩ ነው።


ሌተናል ጄኔራል አስራት በሥልጠናው ቆይታቸው ከፍተኛውን ውጤት ላመጡት መሠረታዊ ተመራቂ ወታደሮችና አሰልጣኞች የተዘጋጀውን ሽልማት እንደሚያበረክቱና የሥራ መመሪያም እንደሚሰጡ ይጠበቃል።


በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ መከላከያ ሠራዊት አዛዦች ፣የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድና የካቢኔ አባላት እንዲሁም የክልሎች ፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም