የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ረገድ “ሙያዊ ጀግንነትን አስመዝግበዋል”-አቶ ጃንጥራር አባይ

1045

ሀምሌ 16 /2013 (ኢዜአ) የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ረገድ “ሙያዊ ጀግንነትን አስመዝግበዋል” ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከከተማዋ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከል ሂደት ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ክብካቤ ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል።

በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ  ዘርፈሸዋል ንጉሴ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ  ጃንጥራር አባይ፡ የከተማዋ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳሉት የጤና ባለሙያች ለህይወታቸው ሳይሰስቱ የቫይረሱን ወረርሽኝ በመከላከል ብሎም ስርጭቱን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።

በዚህም የጤና ባለሙያዎች ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።

የጤና ባለሙያች የጤና ክብካቤ ሰራተኞች የኮሮ ናቫይረስ ስርጭትን በመከላከል ረገድ “ሙያዊ ጀግንነት አስመዝግበዋል” ነው ያሉት።

ከጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ የጽጥታ ተቋማት፣የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ቫይረሱን በመከላከል ረገድ ላበረከቱት አስተዋህጾ ምስጋና አቅርበዋል።

የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመካለከልና የአግልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ ረገድ ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንዲወጡም አቶ ጃንጥራር ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎች ሙያዊ ቃል ኪዳናቸውን  ቫይረሱ በመከላከል ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ወሪርሽኙን በመከላከል ሂደት ላይ የህይወት መስዋትነት ለከፈሉ የጤና ባለሙያዎችና ክብካቤ ሰራተኞች  በቢሮውና መዲናዋ ነዋሪዎች ስም መፅናናትን ተመኝተዋል።

ቫይረሱን በመከላከል ሂደቱ ላይ ተሳትፎ ለነበራቸው ባለድርሻ አከላት ምስጋና አቅርበው፤ ወረርሽኙን የመከላከል ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

እውቅና የተሰጣቸው ባለሙያዎችና የተቋማት ተወካዎች በበኩላቸው እውቅናው ለበለጠ ስራ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል።

ዶክተር ፍቃዱ አብዲሳ ከየካቲት 12 ሆስፒታል  ጤና ባለሞያዎች ላበረከቱት አስተዋህጾ የተሰጠው እውቅና  ከፍተኛ ደስታ  እንደተሰማው ሲያስረዳ የጤና አገልገሎት ስራ ላይም የተሻለ ውጤት ለማምጣት በሞራልም እንደ ስንቅ የሚሆን ነው ብሎታል

ወይዘሪት ፎዚያ ሰይድ ከሚሊኒዬም ጤና ጣቢያ በበኩሏ ሁሌም ጤና ባለሙያ እንደወታደር ፊትለፊት ህይወቱን ሰውቶ እያገለገለ  መሆኑ በመታወቁ ለቀጣይ ስራ አበረታች ነው ብላለች።