የቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዎች የአሸባሪውን ጁንታ ቡድን ትንኮሳና ሴራ በተባበረ ክንድ ለማክሸፍ መዘጋጀታቸውን በሰልፍ ገለጹ

97

ግምቢ ሀምሌ 16 /2013 (ኢዜአ)---በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዎች የአሸባሪውን ጁንታ ቡድን ትንኮሳና ሴራ በተባበረ ክንድ ለማክሸፍ መዘጋጀታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገለፁ።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ 2ተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ  ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

"የህዝቦችን አንድነት በመከፋፈል ከውጪ ጠላትና ከወስጥ ባንዳዎች ጋር በማበር የሃገርን ህለውና ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እየሰራ ያለውን የጁንታ ርዝራዥ ለማጥፋት በአንድነት እንቆማለን " ሲሉ ሰልፈኞቹ አቋማቸውን ገልጸዋል ።

የቆንዳላ ወረዳ ነዋሪ አቶ ዘካሪያስ ጳውሎስ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት "የሀገር ክህደት በመፈፀም  ሀገርን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የጁንታው ርዝራዥ ፍላጎቱ ህልም ሆኖ ይቀራል እንጂ አይሳካለትም" ብለዋል።

የቡድኑን የጥፋት ተልእኮ ለማስቆም ከመከላክያ ጎን ለመቆም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ኦብሳ ዋቁማ በበኩላቸው  የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበርና  የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ መስዋትነት እየከፈለ ከሚገኘው ጅግናው የሀገር መከላክያ ሰራዊት ጎን በሚያስፈልገው ሁሉ ለመቆም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

"ታላቁ ኢትየጵያ ህዳሴ ግድብ 2ተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በድል በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ "ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚፈለግብኝን  ለማድረግ ዝግጁ ነኝ" ብለዋል።

የቆንዳላ ወረዳ ምክትል አስተዳደሪ አቶ ጣሐ ቡላ በበኩላቸው ኢትዮጵይ በለውጥ ጎዳና ላይ መገኘቷ የማይዋጥላቸው  የውጭ ጠላትና የውስጥ ባንዳዎች ሀገር ለማፍረስ ቀንና ሌሊት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

"ይሁን እንጂ ህዝቡ ከለውጥ አመራሩ ጋር በመሆን የጥፋት ሃይሎችን ተንኮልና ሴራ በማክሸፍ ሀገሪቱን ወደፊት እያራመዳት ይገኛል"  ያሉት ምክትል አተዳዳሪው የሴረኞችን እኩይ ተግባር ለመመከት ህዝቡ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

በቆንዳላ ወረዳ የህዳሴ ግድብ የህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተወካይ ወይዘሮ  ፈቲያ አብዱራማንው በወረዳው ለህዳሴ ግድብ ግንባታ በአንድ ሳምንት በቦንድ ግዥ 440ሺህ 500 ብር ድጋፍ መሰብሰቡን በሰልፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል።

"የህዳሴ ግድብ  2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ለሃገሪቱ ትልቅ ድል ነው" ያሉት ሀላፊዋ  የወረዳው ህዝብ የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም