ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ና አሸባሪውን ህወሓት ለማውገዝ ሰልፍ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

74

ሀዋሳ ፤ሐምሌ 14/2013 (ኢዜአ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከ ፍጻሜው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደግፍና አሸባሪውን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ከሲዳማ ክልል የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በዚሁ ሰልፍ  የህዳሴው ግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው እና ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የሚገልጹ መፈክሮችን  እያሰሙ  ይገኛሉ።


በሌላ በኩል በአሸባሪው ህወሓት እና ተባባሪዎቹ የተቃጣብንን ጥቃት ለመመከትና  ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን ለመሆን መዘጋጀታቸውን፣ በሚያስፈልገው ሁሉ   ከመንግሥታችንና  መከላከያ ሠራዊታችን ጎን  በመቆም የኢትዮጵያን  አሸናፍነት  እንዲረጋገጥ ቆርጠን ተነስተናል ሲሉ  ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።

የኢትዮጵያውያን  ሠላምና አንድነት የሚፈታተነውን  ጁንታ ለመጨረሻ ጊዜ  ለማንበርከክ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆማቸውንም እንዲሁ።

ሰልፈኞቹ "ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሀናችንን ለማድመቅ እንሠራለን፣ የአሸባሪውን የህወሓት  ትንኮሳ እናከሽፋለን፣ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ኃያል ሃገር ናት"  የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙይገኛሉ።

"ምዕራባዊያን እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ ያንሱ፣ የትግራይ ህዝብ አጋራችን ነው ፤ጁንታው ጠላታችን ነው" የሚሉ መፈክሮች ከፍ ብለው ተደምጠዋል።

"እኛን ሊለያይ፣ ሊበትን የሚችል ኃይል የለም፣ አይኖርምም" ሲሉ ሰልፈኞቹ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና  ሌሎችም አመራሮች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም