ፋሲል ከነማ 3 አዲስ ተጫዋቾችን ሲያፈርም የ5 ተጫዋቾች ውል አድሷል

239

ሐምሌ 13 / 2013 (ኢዜአ) ፋሲል ከነማ የክረምቱ የተጫዎቾች ዝውውር ከተከፈተ ጀምሮ 3 አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያፈርም የ5 ተጫዎቾቹን ውል አድሷል።

ፋሲል ከነማ በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየሪሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ነው።

ለአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታና ለቀጣዩ ዓመት ቤትኪንግ ፕርሚየሪሊግ ራሱን ለማጠናከር ሶስት አዳዲስ ተጫዎቾችን ከተለያዩ ክለቦች አስፈርሟል።

ክለቡ በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር አስቻለው ታመነ እና አብዱልከሪም ሙሀመድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኦኬኬ አፎላቢን ከሲዳማ ቡና አስፈርሟል።

አዳዲስ ተጫዎቾችን ከማስፈረሙ በተጨማሪም በክለቡ የሚጫወቱ አምስት ተጫዎቾችን ውል አድሷል።

ከእነዚህ መካከል ኪሩቤል ሀይሉ፣ ሚካኤል ሳማኪ፣ ከድር ኩሊባሊን እና ዳንኤል ዘመዴ ይገኙበታል።

በተጨማሪም ክለቡ ትናንት ወጣቱን ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን ለተጨማሪ ሶስት ዓመት የሚያቆይ ውል ተፈራርሟል።

የዚህ ዓመት የክረምት የተጫዎቾች የዝውውር ጊዜ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን በአፍሪካ መድረክ የሚካፈሉ ክለቦች ግን ሐምሌ ከመግባቱ በፊት ጀምሮ ተጫዎቾችን ማስፈረም እንደሚችሉ በፌደሬሽኑ ፍቃድ ማግኘታቸውን ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም