ብሔራዊ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ነው

123

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 8/2013 (ኢዜአ) ብሔራዊ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ነው ።

በመድረኩ የብሔራዊ ባንክ አመራር አባላት የተባበሩት መንግስታት የልማት የካፒታል ፈንድና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርዓትና ሴትልመንት ዳይሬክተር ወይዘሮ ማርታ ሀይለማርያም እንዳሉት የዲጅታል ክፍያ አገልግሎት ከግለሰብ ጀምሮ እስከ መንግስት ባሉ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ የሚጫወተው ሚና ጉልህ ነው ።

የዲጅታል ክፍያ አገልግሎት በኢትዮጵያ በጅምር ላይ መሆኑን ተናግረው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ክፍያን በቀላል፣በአነስተኛ ወጪ እና ጊዜ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለመፈፀም ይረዳል ነው ያሉት።

የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን እርካታ መጨመር እና የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለአገራዊ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አንስተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም