በምዕራብ ወለጋ ዞን በአንድ ጀምበር 22 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል - ኢዜአ አማርኛ
በምዕራብ ወለጋ ዞን በአንድ ጀምበር 22 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል
ግምቢ፣ ሐምሌ 05 ቀን 2013 (ኢዜአ) የምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪዎችን በማሳተፍ በአንድ ጀምበር 22 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ነገ በሚካሄደው በዚሁ መርሃ ግብር በዞኑ በ23 ወረዳዎች የሚገኙ ከ446 ሺህ ሰዎች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብረሃም ደሜ ተናግረዋል፡፡
"ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከብ ለውጤት ማብቃት አለብን" ያሉት አቶ አብረሃም፤ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ አገራዊ ልማትን ለመደገፍ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡ የአረንጓዴ ልማት ጠቀሜታን በመረዳት ንቁ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።