ቀጥታ፡

የመጀመሪያው የትምህርት ምርምር፣ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ትስስር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/2013 (ኢዜአ) የመጀመሪያው የትምህርት ምርምር፣ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ትስስር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ "ወደ ዕውቀት-መር ኢኮኖሚ" በሚል መሪ ሃሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ/ም የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

በሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተሠናዳው ጉባኤ የሣይንሣዊ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን የማስተዋወቅ እንዲሁም በስራ ላይ እንዲውሉም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ ተብሏል።

ለምርምርና ቴክኖሎጂ ልማት እንቅስቃሴ የሚያግዙ የእርስ በርስ ትስስርና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጠናከር ማድርግም የኮንቬንሽኑ ዋነኛ ዓላማ መሆኑ ተመለክቷል።


የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ማበረታታት፣ እውቅና መስጠትና የከፍተኛ ትምህርት ጥናትና ምርምር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውጤታማነትን ማረጋገጥም አይነተኛ ግቦች ሆነው ተቀምጠዋል።

በኮንቬንሽኑ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሣሙኤል ኡርቃቶ አና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊች ተገኝተዋል።


የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣ ተመራማሪዎችና የኢንዱስትሪ መሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም