የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም አገራት በበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን በመሆኑ የዘመናችን ዋነኛ ተግዳሮት ሆኗል ... ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ - ኢዜአ አማርኛ
የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም አገራት በበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን በመሆኑ የዘመናችን ዋነኛ ተግዳሮት ሆኗል ... ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ሐምሌ 2/2013(ኢዜአ) የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም አገራት በበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን በመሆኑ የዘመኑ ዋነኛ ተግዳሮት ሆኗል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቷ ይሄን ያሉት በባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር በተሰበሰበና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስፈልገዉን ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ኢትዮጵያ በጣም ተጋላጭ እንደመሆኗ መጠን በተለያዩ የጋራ እና ብሄራዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የህብረተሰቡን የመቋቋም አቅም ለማሻሻል እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ገልጸዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ያባባሰ ሲሆን ሁለቱም የተቀናጀ እና ፈጣን የጋራ እርምጃን እንደሚጠይቁም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ያደጉ አገራትም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የድርሻቸውን ፍጥነት እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውንም ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።