የፀጥታው ምክርቤት አባላት የህዳሴው ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሊቀጥል እንደሚገባ ገለፁ

ሀምሌ 01 ቀን 2013 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የህዳሴው ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በግብጽ ፍላጎት ስብሰባ የተጠራው የፀጥታው ምክርቤት አባላት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ መክሯል፡፡

በዚህም አሜሪካን ጨምሮ የበርካታ አገራት ተወካዮች የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ባከበረ መልኩ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል።የአሜሪካ፣ ሩሲያ፣ አየርላንድ፣ እንግሊዝ፣ ሜክሲኮ፣ ህንድና ኬንያ ድርድሩ በአፍርካ ህብርት እንዲቀጥል ፍላጎት ካሳዩ ተወካዮች መካከል ናቸው፡፡

በመሆኑም ጉዳዩ ዕልባት ማግኘት ያለበት ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሚያደርጉት ውይይት እንጂ በሌሎች ሀገራት ጣልቃ ገብነት ሊሆን አይገባም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ተወካዮች ንግግር ያደረጉነ ሲሆን የኢፌዲሪ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ባደረጉት ንግግር ግድቡ እየተገነባ ያለው በኢትዮጵያን ደም፣ ላብና ና እንባ መሆኑን ጠቁመው ግድቡ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ጉዳዩ የሚመለከተው የአፍሪካ ህብረትን በመሆኑ በጀመረው መሰረት ሚናውን እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም