ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን ወክለው በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚወዳደሩ አትሌቶችን ዝግጅት በልምምድ ስፍራ ተገኝተው ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30/2013 ( ኢዜአ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን ወክለው በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚወዳደሩ አትሌቶችን ስልጠና እና ዝግጁነታቸውን በልምምድ ቦታ ላይ ተገኝተው በመመልከት አበረታቱ።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የበላይ ጠባቂ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተገኝተው የተወዳዳሪዎችን ዝግጅት ተመልክተዋል።

ተወዳዳሪዎችም የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አበረታተዋቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም