የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ከሶስት በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ማስፈረም እንደማይችሉ ውሳኔ ተላለፈ

74

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29/2013 (ኢዜአ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ከሶስት በላይ የውጭ ሀገር ተጫዎቾችን ማስፈረም እንደማይችሉ ውሳኔ ተላለፈ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ዝውውር አስመልክቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በውሳኔውም የ2014 የቤትኪንግ የኘሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ከሶስት በላይ የውጭ ሀገር ተጫዎቾችን ማስፈረም እንደማይችሉ ነው ያስታወቀው።

የከፍተኛ ሊግና አንደኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ደግሞ ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን እንዳያስፈርሙ ውሳኔ ተላልፏል።

በፕሪምየሪ ሊጉ የሚሳተፉ ክለቦች ከዚህ በፊት እስከ አምስት የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ማስፈረም ይችሉ ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም