ኢትዮ ቴሌ ኮም የአራተኛ ትውልድ አገልግሎት በደቡብ ሪጅን የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እያካሄደ ነው

132

ሀዋሳ፤ ሰኔ 29/2013 (ኢዜአ )ኢትዮ ቴሌ ኮም የአራተኛ ትውልድ / 4ጂ/ ኢንተርኔት አድቫንስድ አገልግሎት በደቡብ ሪጅን የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።

አገልግሎቱ በሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌና ዲላን ጨምሮ በሪጅኑ 12 ከተሞችን እንደሚሸፍን በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በዚሀም አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመልክቷል።

በስነ-ስርዓቱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም