በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

79

ሰኔ 24 ቀን 2013 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ አካላት፣ የየዩኒቨርስቲዎች አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን ጉዳዩን እየሰራበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተደረገው ጥረትም የዩኒቨርቲዎችን አመራር ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ናቸው ብሏል ሚኒስቴሩ።

ስለሆነም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ተረድተው በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሚኒስቴሩ በቀጣይ ተማሪዎች ፈተና ወስደው ሲጨርሱ የሚኖሩ ጉዳዮችን እንደሚያሳውቅ ገልጾ፤ የተማሪ ወላጆች በመደበኛ መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ መረጃዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ እና ተረጋግተው እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም