ተመድ ሀገራት የዘረኝነት ተግበራትን ከመደበቅ እንዲቆጠቡ አሳሰበ

75

ሰኔ 21 ቀን 2013 (ኢዜአ) ሀገራት የዘረኝነት እንቅስቃሴዎችን ከመደበቅ እንዲቆጠቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ አቅርቧል።

ጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈጸመ አይነት ወንጀል እንዲሁም ጥቁር ጠል የሆኑ የዘረኝነት እንቅስቃሴዎችንና ጥቃቶች እንዳይደገሙ ለማድረግም ሰኞን ስልታዊ የጸረ-ጥቁር ዘረኝነት እንቅስቃሴ ቀን ብሎ መሰየሙን መረጃው አመላክቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘረኝነት እንቅስቃሴዎች በየሃገራቱ እየተካሄደ እንደሆነ በመግለጽ ሀገራት እንዲህ አይነት እንቅስቃሴዎችን መደበቅ የለባቸውም ብሏል፡፡

ሀገራት የጥቁር ጠል ዘረኝነት እንቅሳቀሴን የማይከላከሉ ከሆነ በመላ ዓለም የጆርጅ ፍሎይድ አሟሟት አይነት ወንጀሎች ሊበራከቱ እንደሚችሉ ስጋቱን ገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ሚቼል ባሽሌት በዓመት ውስጥ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎችን የተመለከተ ሪፖርት ዛሬ ሰኞ ባቀረቡበት ወቅት ይህን ጥሪ ማቅረባቸውን ሲጂቲኤን በዘገባው አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም