ምክር ቤቱ ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ630 ሚሊዮን ብር በላይ በጀትና የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ጉባውን አጠናቀቀ

ሰመራ ሰኔ 20/2013 (ኢዜአ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ630 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀትና የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ዛሬ አጠናቀቀ።

የክልሉ ምክር ቤት ትናንት የተጀመረውን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በበጀት አመቱ በክልሉ ለተከናወኑ መደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 630 ሚሊዮን 241ሺ 375 ብር ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ ዛሬ አጠናቋል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም የተለያዩ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ሃላፊነት ለመደንገግ የወጡ ሶስት ተጨማሪ አዋጆች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።


በምክር ቤቱ ከጸደቁት አዋጆች ውስጥ በክልሉ ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ ረቂቅ አዋጅና የክልሉን የልማት ድርጅቶች አመሠራረት፣ አደረጃጀት ፣አመራርና ድጋፍ አሠጣጥን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ይገኝበታል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ በአዋጆቹ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ስራ ላይ እንዲዉሉ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ እስቸኳይ ጉባኤውን ተጠናቋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም