ሜሪጆይ ኢትዮጵያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል በሆሳዕና ከተማ ሊያስገነባ ነው

ሆስዕና፤ ሰኔ 10/2013 (ኢዜአ) ሜሪጆይ ኢትዮጵያ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ 50 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ለሚያስገነባው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

ማዕከሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ300 በላይ   አረጋውያን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችል በመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡ ሰነ-ስርዓት ወቅት ተገልጿል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣የሜሪጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ኃላፊዎችና አርቲስቶች ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም