ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተጋብዘው በሰላም ዙሪያ ንግግር እንዲያደርጉ ተጠየቀ

93
አዲስ አበባ ሐምሌ 27/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ግብዣ ተደርጎላቸው ገለፃ እንዲያደርጉ በድርጅቱ የስዊድን አምባሳደር ኦሎፍ ስኩግ ጠየቁ። ስዊድን በምክር ቤቱ የነበራትን የፕሬዝዳንነት ኃላፊነት ማብቃት ተከትሎ በምክር ቤቱ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አምባሳደሩ እንደተናገሩት፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ለ20 ዓመታት የዘለቀውን የኢትዮጵያና ኤርትራ አለመግባባት ለመፍታት ተጨባጭ ጥረት አላደረገም። ሆኖም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን እንደ መጡ የሰላም መፍትሄ አበጅተው በሁለቱ አገሮች መካከል ግንኙነቱ መሻሻሉን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብዣ ተደርጎላቸው በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ገለፃ ቢያደርጉ የሌሎች አገሮች መሪዎች ስለ ሰላምና ደህንነት ትልቅ ትምህርት ሊያገኙ ይችላሉ መባሉን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም