እየተገነባ ያለውን የፍቅር ድልድይ ከዳር ለማድረስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

65
አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2010 በአገሪቱ እየተገነባ ያለውን የፍቅር ድልድይ ከዳር ለማድረስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ጠየቀ። ጽህፈት ቤቱ በሳምንታዊ የአቋም መግለጫው እንዳመለከተው፤  በውጭ የሚኖሩ ወገኖች የተጀመረውን የይቅርታ ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የመደመር ጉዞ በመምረጥ ለልዩነት ግንቡ መፍረስ እና ለአዲሱ የፍቅር ድልድይ መገንባት ላበረከቱት አስተዋጽኦ መንግሥት ምስጋናውን አቅርቧል። በውጭ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሁለንተናዊ ልማት እና ብልጽግና ያሳዩትን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር በመለወጥ እውቀታቸውን እና ገንዘባቸውን ለአገር ግንባታ ለማዋል እንዲረባረቡ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል። የኃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ኃይሎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና ሴቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች በአጠቃላይ መላው ህዝብ መገንባት የተጀመረውን የፍቅር ድልድይ ከዳር ለማድረስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል። መግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ ያገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም