የኢትዮ ቴሌኮም በድሬዳዋ የ4ጂ አገልገሎት ጀመረ

ግንቦት 17/2013(ኢዜአ) ኢትዮ ቴሌኮም በድሬዳዋ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል᎐ቲ᎐ኢ አድቫንስንድ አገልግሎት ጀመረ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ማምሻውን በድሬዳዋ የ4ጂ አገልግሎት መጀመሩን ባበሰሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፤ የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ የኢንተርኔት መሠረተ ልማት በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ተዳራሽ ሆኗል።
በዚህም ድሬደዋ ፣በሱማሌ ክልል አይሻ እና በኦሮሚያ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተሞች የሚገኙ 330ሺህ ደንበኞች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ እና ሌሎች ጥቂት የሀገሪቱ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረው ይሄው አገልግሎት ወደ 103 የክልል ከተሞች ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል ።
አገልግሎቱ ከቀደሞ የ3ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ሆኖ ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ የምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ አግልግሎቶችን ትርጉም ባለው መንገድ ያቀላጥፋል ብለዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምከትል ከንቲባ አህመድ መሐመድና የካቢኔ አባላት ፣ባንኮች፣ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትና የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም