ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 398 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

66

ሆሳዕና፣  ሚያዝያ 30/2013 (ኢዜአ) ዋቸሞ ዩንቨርስቲ በሆሳዕናና በዱራሜ ካምፓሶች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 398 ተማሪዎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እያስመረቀ ነው።
 

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ እያስመረቃቸው ካሉ ተማሪዎች ውስጥ 23ቱ በሁለተኛና ቀሪዎቹ በአንደኛ ዲግሪ የተሰጣቸውን ስልጠና በአግባቡ ያጠናቀቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ ተከታታይ መርሀ ግብር በማህበራዊ ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በቴክኖሎጂና በግብርና ዘርፎች የሰለጠኑ ናቸው።


በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ተስፋዬን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም