አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ ከዛሬ ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገለጸ

67

ሚያዚያ 25/2013 (ኢዜአ) አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከዛሬ ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በአካል ቅሬታ የሚያቀርቡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ገልጿል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ምደባ ሚያዚያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በዚሁ መሰረት የተመደቡ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከሚያዚያ 25 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረብ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው በሚኒስቴሩ ድረ ገጽ፣ የኢ-ሜይል እና በስልክ አድራሻዎች ማቅረብ እንደሚችሉ አመልክቷል።

ተማሪዎች በድረ-ገጽ https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7፣ በስልክ ቁጥር +251911763794 እና +251943543805 እንዲሁም የኢ-ሜይል አድራሻ support@ethernet.edu.et ቅሬታ የሚያቀርቡባቸው አማራጮች መሆናቸው ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአካል ቅሬታ የሚያቀርቡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ አስታውቋል።

አዲስ የተመደቡት ተማሪዎች በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የነበሩ ቢሆንም ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱ ሳይሰጥ በመቆየቱ በ2013 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ ፈተናውን እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም