በጉጂ ዞን ከ592 ሺህ በላይ ህዝብ የምርጫ ካርድ ወሰደ

ነገሌ፤ ሚያዝያ 22/2013 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክለል a ጉጂ ዞን እስካሁን ከ592 ሺህ በላይ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቦ የምርጫ ካርድ መውሰዱን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዞኑ ማስተባበሪያ ገለጸ።

የማስተባበሪያው ምክትል ሀላፊ አቶ ስራው በቀለ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤  በዞኑ በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ መራጮችን ለመመዝገብ ከአንድ ሺህ 640 በላይ ምርጫ አስፈጻሚዎች ተመድበዋል፡፡

በአስፈጻሚዎቹ አማካኝነት በዞኑ በተቋቋመ  547 ምርጫ ጣቢያዎች  700 ሺህ 212 ህዝብ በመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቁው  እስካሁን 592 ሺህ 307  ካርድ መውሰዱን  ገልጸዋል።

ተመዝግበው የምርጫ ካርድ ከወሰዱት መካከል   ከ251ሺህ በላይ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የዞኑ ህዝብ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚመሩትን እጩዎች ለመምረጥ እስካሁን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለመራጮች ምዝገባ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ሳምንት ያህል የቀረው በመሆኑ በበዓላት ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ምዝገባው ቢቋረጥም ሚያዚያ 25/2013ዓ.ም  ስለሚቀጥል የምርጫ ካርድ ያልወሰደው ህዝብ  ተወካዮዎቹን መምረጥ እንዲችል በወቅቱ እንዲመዘገብ  መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የመራጭነት ምዝገባ ቀን እስከ ሚያዝያ 29/2013 ዓ.ም መራዘሙ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም