ብልጽግና ፓርቲ በደቡብ ጎንደር የማኒፌስቶ ትውውቅና የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ነው

59

ሚያዝያ 21/2013 (ኢዜአ) ብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የማኒፌስቶ ትውውቅና የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ነው።

በጎዳና ላይ ቅስቀሳው ላይ ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ቀለመወርቅ ምህረቴ፣ በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተገኝተዋል። “ፅንፈኝነት እና ጥላቻ የአማራ ህዝብ እሴት አይደለም”፣ “ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሆነው ብልፅግና ይቅደም”፣ “ብልፅግና የገጠሙንን ችግሮች ሁሉ መፍቻ መንገድ ነው”፣ “እኛ ብልፅግናዎች ሀገራችን ወደ ማትወርድበት ከፍታ ሳትወጣ ወደ ኋላ አንመለስም” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች እየተሰሙ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አገኘ ተሻገር በሰላሞዊ ሰልፍ ለተሳተፉት መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎም ይጠበቃል::


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም