ሲኖቫክ የተሰኘው ክትባት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞትን 80 በመቶ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ - ኢዜአ አማርኛ
ሲኖቫክ የተሰኘው ክትባት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞትን 80 በመቶ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ
74
ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም(ኢዜአ)በቻይና የተመረተው ሲኖቫክ የተሰኘው ክትባት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞትን በ80 በመቶ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመልክቷል።
ጥናቱን ያከናወኑት የቺሊ ተመራማሪዎች ሲሆኑ በውጤቱም በቻይና የተመረተው ሲኖቫክ የተባለው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞትን 80 በመቶ እንደሚቀንስ ዥንዋ ዘግቧል፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ከሆነ ክትባቱ የተላላፊ በሽታዎችን 67 በመቶ እንደሚከላከል እንዲሁም በሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ ሰዎችን ደግሞ በ85 በመቶ ይቀንሳል፡፡
ክትባቱ በቫይረሱ ክፉኛ ተጎድተው በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገቡ ሰዎች መካከልም 89 በመቶ የሚሆኑትን እንደሚያድን የጥናት ውጤቱ ጠቁሟል፡፡