የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ ጀመሩ

59

ሚያዚያ 10 / 2013 (ኢዜአ) የሕዳሴ ግድብ ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ተጠናቅቀው ስራ መጀመራቸውን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ሁለቱ የውሃ ማስተንፈሻዎች ግንባታ ተጠናቀው ስራ ጀምረዋል፡፡

ሁለቱ ማስተንፈሻዎች አጠቃላይ ዓመታዊውን የዓባይ ፍሰት የማሳለፍ አቅም እንዳላቸው ተመልክቷል፡፡

ማስተንፈሻዎች በግድቡ ሙሌት ወቅት የዓባይ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ያለውን ፍሰት እንዲጨምር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

በዚህም ወደ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት የሚኖረውን የውሃ ፍሰት እንደማያስተጓጎል ማረጋገጫ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም