የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የህዘቦችን ሰላምና አንድነት ለማጠናከር እንዲውል ይሰራል- ዶክተር ሂሩት ካሳው

142

ሐረር፤ ሚያዚያ 9/ 2013ኢዜአ) የባህልና ቱሪዝም ዘርፍን በማጎልበት የህዝቦችን ሰላም ፣ እርስ በርስ ግንኙነትና አንድነት ለማጠናከር እንዲውል ለማድረግ እንደሚሰራ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ገለጹ።

የሚኒስቴሩ የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት  እቅድ አፈጻጸም ጉባኤ  በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው መድረክ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለጹት ፤ በቀጣይ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍን አጎልብቶ ሰላምን በማምጣት የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነትና አንድነት ለማጠናከር እንዲውል ይሰራል።

ዘርፉ የህዝቦችን ፍቅር፣ ትብብርና መደጋገፍን ለማጎልበት  ጭምር ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ጉባኤው  ከሀገራዊ ሁኔታዎች አንጻር ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን እገዛ ያደርጋል ብለዋል::

በህዝቦች መካከል አንድነትን፣ፍቅርንና ትብብርን እንዲጎለብት እና የአገሪቱ ሰላም እንዲጠናከር ከማድረግ አንጻር ሴክተሩ ሚናውን በተሻለ ደረጃ እንዲወጣ ለማድረግም ጉባኤው የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በዚህም ያሉ ልምዶችንና ጥንካሬዎችን ለመጠቀም እንዲሁም በክፍተቶች ላይ በቅንጅት ለመስራት እድል ይፈጥራል ብለዋል።

የሐረሪ ክልል ባህል ፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን በበኩላቸው፤ ጉባኤው ክልሎች የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዙ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ጉባኤው በተለይ በክልሉ መካሄዱ በአካባቢው የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅና ልምዶችን ለመለዋወጥ ያግዛልም ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት  የስራ አፈጻጸም ፣ የክትትልና ድጋፍ ሪፖርት እንደሚቀርብ ተመልክቷል።

በጉባኤው የክልል ባህልን ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊዎች ፣ በህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት የሴቶች ፣ወጣቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም አካላት እየተሳተፉ ነው።

በተጓዳኝም  የጀጎል ግንብ የቱሪስት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጪያ ማዕከል ምረቃ ስነ-ስርዓት እንደሚከናወንም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም