በ2010 በጀት ዓመት ከውጭ አገር ጎብኚዎች 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

128
አዲስ አበባ ሀምሌ 24/2010 በ2010 በጀት ዓመት ኢትዮጵያን ከጎበኙ 934 ሺህ ጎብኚዎች 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ። በ2004 ዓ.ም አፍሪካን ከጎበኙ 52 ነጥብ 3 ሚሊዮን ጎብኚዎች 34 ቢሊዮን ዶላር ሲገኝ ከዚህ ወስጥ ኢትዮጵያን የጎበኙት 596 ሺህ 341 ብቻ  ሲሆኑ የተገኘው ገቢ ደግሞ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ብቻ ነበር። በ2009 በጀት ዓመት ኢትዮጵያን ከጎበኙ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የጎብኚዎች ቁጥር ወደ 934 ሺህ የተገኘው ገቢም ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ አባተ ለኢዜአ እንደተናገሩት የጎብኚዎች ቁጥርና ገቢ ካለፉት ዓመታት ብልጫ አለው።   ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱ ከ177 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል እንደፈጠርም ገለጸዋል። እንደ አቶ ገዘሃኝ ገለጻ የቱሪዝም እንቅስቀሴው በመጀመሪዎቹ እና በሁለተኛ የሩብ ዓመት ጥሩ ቢሆንም በመጨረሻው ላይ ግን በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ተቀዛቅዞ ነበር። በኢትዮጵያ የተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች ቢኖሩም አሁንም ዘርፉ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑንም አቶ ገዘኸኝ ጠቁመዋል። በቂ መሰረተ ልማት አለመኖር፣ዝቅተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች ተግዳሮቶች ጎብኚዎች የቆይታቸውን ጊዜ እንዳያራዝሙ ማነቆ ሆኗል ብለዋል። ሚኒስትሩ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከመንግስትና ከባለሀብቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቅርስ መዝጋቢ ተቋም ዩኔስኮ ባስመዘገበቻቸው ቅርሶች ብዛት ቀዳሚ ብትሆንም በአፍሪካ በብዛት ከሚጎበኙ አገራት መካከል 17ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያን በ2012 ዓ.ም መጨረሻ በአፍሪካ በቱሪስት መዳረሻነት 5ኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑ አይዘነጋም።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም