በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲሳካ የኢትዮጵያ ጥረት ይቀጥላል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

643

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7/2013 (ኢዜአ) በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲሳካ የኢትዮጵያ ጥረት የሚቀጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ ሳምንታዊ አበይት ክንውኖች በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። 

በመግለጫቸውም የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በመሪዎች ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ላቀረቡት ጥያቄ በኢትዮጵያ በኩል በይፋ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡ 

ኢትዮጵያም ጉዳዩን አጢና ምላሽ የምትሰጥ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ አፍሪካ ህብረት የሚመራው ድርድር ውጤታማ እንዲሆን ትፈልጋለችም ብለዋል፡፡

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት የጀመረውን የሶስትዮሽ ድርድር እንዳይሳካ ግብጽ ጥረት እያደረገች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡