ዶክተር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተሾሙ

61

ሚያዝያ 7/2013(ኢዜአ) ዶክተር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ መሾማቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዶ/ር ፋና የመጀመሪያ ድግሪያቸዉን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት የተቀበሉ ሲሆን ሁለተኛ ድግሪያቸዉን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሪስቴትና ሶስተኛ ድግሪያቸዉን በዋርዊክ ዩኒቨርስቲ ተምረዋል።

በመቀጠልም ኬኒያ ናይሮቢ በሚገኘዉ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ የፖስት ዶክተሬት ተመራማሪ ሆነዉ ሰርተዋል።

ፕሬዝዳንቷ ስራ የጀመሩት በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ-ህግ በመሆን ሲሆን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ለአስራ ሁለት አመታት የህግ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን አገልግለዋል።

በዩኒቨርስቲዉ የስርዓተጾታ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና የህግና ስነ-መንግስት ኮሌጅ ዲን በመሆንም አገልግለዋል።

ሹመቱ ከጥቂት ዓመታት በፊት በዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸዉን የሴቶችን ተሳትፎ አንድ እርምጃ የሚያሳድግና ወጣት ኢትዮጵያዊያንንም ያነቃቃል ነው የተባለው።

ዶ/ር ፋና በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት ከመሾማቸዉ በፊት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ እንደነበር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም