ኬንያ በኮቪድ-19 ምክንያት የጣለችውን የሰዓት እላፊ ገደብ እስከ ግንቦት መጨረሻ አራዘመች

82

ሚያዚያ 06 /2013 (ኢዜአ) በኬኒያ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውና በኮቪድ-19 ምክንያት የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ እስከ ግንቦት መጨረሻ እንዲቀጥል መደረጉን የኬንያ የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ዶ/ር ፍሬድ ማቲያንጊ እንደገለጹት መንግስት ባወጣው የሰዓት እላፊ ገደብ መመሪያ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ በእጅጉ በተስፋፋባቸውና በከፋባቸው የናይሮቢ ከተማና ሌሎች አራት አካባቢዎች ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድም።

በሌሎቹ አካባቢዎች ደግሞ ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት በሚል የተጣለው ገደብ እንደተጠበቀ እንደሚገኝ ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል።

“ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ይቆያል” በሚል ፕሬዝዳንቱ አወጡት የተባለው የእንቅሰቃሴ እቀባ መቼ እንደሚነሳ ሳይታወቅ ቆይቶ ነበር ያለው ዘገባው በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ሀገሪቱ ካለፈው አመት መጋቢት ወር ጀምሮ በተለያዩ የሰዓት እላፊ ገደቦች ውስጥ መሆኗ ነው የተገለጸው።

ካለፈው መጋቢት ወር አንስቶ የአገሪቱን መዲና ናይሮቢን ጨምሮ፣ ካጂያዶ፣ ማቻኮስ፣ ኪያምቡና ናኩሩ ባሉ አምስት የኬንያ አካባቢዎች ኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ በመሰራጨቱ ሁሉም አይነት እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ያዘዙት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ናቸው ተብሏል።

ኮሮናን በሚመለከት በየሰዓቱ አሃዛዊ መረጃዎችን የሚያወጣው የወርልዶ ሜትር ድረገጽ እንደሚያስረዳው ከሆነ ከአንድ መቶ 47 ሺህ በላይ ኬንያውያን በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሁለት ሺህ አራትመቶ የሚጠጉት ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ዘገባው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም